በተለያዩ የሠራዊቱ ክፍሎች ሥልጠና ተሰጠ

 

በማዕከላዊ ዕዝ ጤና መምሪያ ለዕዙ ስታፍ የሠራዊት አባላት በኢቮላ በሽታ፣ በአጣዳፊ ተቅማጥ እና ትውከት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ተሰጠ።

ትምህርቱን የሰጡት የማዕከላዊ ዕዝ ጤና መምሪያ ኃላፊ ኮሎኔል ኢሳያስ አሰፋ እንደተናገሩት፤ የኢቮላ በሽታ ሥርጭት በሀገራችን ብሎም በሠራዊታችን እንዳይከሰት ለማድረግ አመራሩ አጋዥ በመሆን እና ለሚመራው አባል ስለ ኢቮላ ምንነት እንዲሁም መተላለፊያ መንገዱን ጭምር ማስረዳት ይጠበቅበታል።

ከፍተኛ መኮንኑ ባስተላለፉት መልዕክት የበሽታ ወረርሽኝ በመጣ ጊዜ ብቻ መሯሯጥ ሳይሆን በሽታው ከመከሰቱ በፊት የግል እና የአካባቢያችንን ንጽህና በመጠበቅ የበኩላችንን ድርሻ መወጣት እንደሚያስፈልግ መናገራቸውን ሪፖርተራችን ሻምበል ሙሉጌታ አለባቸው ዘግቧል።

በተያያዘ ዜና በባሩድ ማዕከላዊ ዕዝ ለ332ኛ ሬጅመንት የሠራዊት አባላት ሲሰጥ የቆየው የቡድን መሳሪያ ሥልጠና ተጠናቋል።

በሥልጠናው ማብቂያ ላይ በመገኘት ሥልጠናውን አስመልክተው ንግግር ያደረጉት የሬጅመንቱ ምክትል አዛዥ ለሎጀስቲክስ፤ ሌተና ኮሎኔል ፋንታየ ወልዱ  እንደተናገሩት ሲሰጥ የቆየው ሥልጠና ለሠራዊታችን የግዳጅ አፈጻጸም አስፈላጊ እና ለወደፊት ለሚኖሩን ግዳጆች የላቀ ጠቀሜታ ይኖረዋል።

የቡድን መሣሪያ የቴክኒክ ሥልጠናውን የሰጡት የሬጀመንቱ ሥልጠና ዴስክ ኃላፊ ም/መ/አለቃ ናርዶስ ወርቁ በበኩላቸው ነባሩን የሠራዊት ክፍል ከአዲሱ የሠራዊት አባል ለማጣጣም እና ተመሳሳይ አቅም እና ችሎታ እንዲኖራቸው ለማድረግ ይረዳል ማለታቸውን የሬጅመንቱ ሪፖርተር ም/!አለቃ ፍቅር ተገኘ ዘግቧል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!
በብዛት የተነበቡ የክቡር የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን የህይወት ታሪክ
የክቡር የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን የህይወት ታሪክ
ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ከአባታቸው ከ፲አለቃ መኮንን ይመር አና ከእናታቸው  ከወ/ሮ ሂይወት ይህደጎ ተላ በትግራይ ክልል በሰሜን ምዕራብ ዞን አስገደ ምጽብላ...
ፋውንዴሽኑ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች ሊያስረክብ ነው
ፋውንዴሽኑ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች ሊያስረክብ ነው
የመከላከያ  ፋውንዴሽን  በመጀመሪያ ዙር ያስገነባቸውን 112 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በቅርቡ ለሠራዊቱ በዕጣ ለማስተላለፍ ዝግጅት መጠናቀቁን የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ዋና ስራ...
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ውጤታማ ስራ ማከናወኑ ተገለጸ
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ውጤታማ ስራ ማከናወኑ ተገለጸ
የመከላከያ ኮንስተራክሽን ኢንተርፕራይዝ  በ2011 የበጀት አመት በርካታ ዉጤታማ ስራዎች ማከናወኑ ተገልጿል፡፡
ኮሌጁ ሶስተኛውን ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ አካሄደ
ኮሌጁ ሶስተኛውን ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ አካሄደ
የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ሦስተኛውን ሀገርአቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ አካሄደ።
ሰኔ 14 10 2011 መከላከያ ሬዲዮ ዜና