“የሠራዊታችን የጀግንነት ምንጭ ህዝባዊነቱ ነው”

 

“የሠራዊታችን የጀግንነት ምንጭ ህዝባዊነቱ ነው” ሲሉ ሜ/ጄኔራል አባዱላ ገመዳ ገለጹ።

ጄኔራል መኮንኑ ይህን የገለጹት ሰሞኑን ከመከላከያ ሚዲያ ጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው።

ህዝብ የኔ ነው የሚለውው ሁል ጊዜም ጀግና፣ አሸናፊና ወደፊት የሚራመድ ነው ያሉት ሜ/ጄኔራል አባዱላ፣ ሠራዊቱ የህዝብ ፍቅር ያለው በህዝቡ ውስጥ የሚኖር፣ ህዝቡንና ህገ-መንግሥቱን የሚጠብቅ ሠራዊት እንደሆነም ተናግረዋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራወዊት በተሰማራባቸው ቀጣናዎች በሙሉ የህዝብን ፍቅር አትርፎ  ግዳጁን በብቃት ፣ በጀግንነትና የኃላፊነት ስሜት ተልዕኮዎቹን በመፈጸም ለሀገር ኩራት እንደሆነም ሜ/ጄኔራል አባዱላ ገልጸዋል።

የሠራዊቱ የጀግንነት ምንጭ የሆነው ህዝባዊነት መንፈስንና በእምነትና በጽናት እየተወጣ ያለውን ህገ-መንግሥታዊ ተልዕኮ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ተናግረዋል።

ተቋሙ እያካሄደ ያለውን የለውጥ አሰራር አጠናክሮ በመቀጠል የዘመናዊ ሠራዊት ግንባታ ሂደቱን ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባም ሜ/ጄኔራል አባዱላ ጠቁመዋል።

የዘመናዊ ሠራዊት ግንባታን አጠናክሮ በመቀጠልና ውጤታማ በማድረግም ሠራዊታችንን ሞዴልና ተመራጭ ሠራዊትነቱን ይበልጥ ማጎልበት እንደሚገባም ጄኔራል መኮንኑ አስረድተዋል።

ክፍለ ጦሩ ተልዕኮን በድል መደምደም የሚችል ሠራዊት መገንባቱን አስታወቀ

በፀጋዬ ገብሬ (ሻምበል)

የጋዜጣው ሪፖርተር

 

 

ፈታኝ የአየር ሁኔታን ተቋቁሞ ተልዕኮን በድል መደምደም የሚችል ሠራዊት መገንባት እንደተቻለ የ36ኛ ክፍለጦር ዋና አዛዥ አስታወቁ።

ዋና አዛዡ ብርጋዲየር ጄኔራል ሙሉ ዓለም አድማሱ ከመከላከያ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ ክፍለ ጦሩ ከዓለም ዝቅተኛ ቦታዎች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀስና ከፍተኛ የሙቀት መጠን ባለው የግዳጅ ቀጣና ተልዕኮውን እየፈጸመ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

“አካባቢው ኤርታሌና ሌሎች የተፈጥሮ መስህቦች የሚገኙበት ስፍራ በመሆኑ፤ ከአራቱም የዓለማችን አቅጣጫ የሚመጡ ቱሪስቶች መዳረሻ ነው” ያሉት ጄኔራሉ የቀጣናውን ሠላም ማረጋገጥና የሀገርን ጥቅም ማስጠበቅ ክፍለ ጦሩ ካነገባቸው ተልዕኮዎች አንዱ መሆኑን ተናግረዋል።

እንደ ጄኔራል መኮንኑ ገለጻ፤ በከፍተኛ ሙቃታማነቱ በሚታወቀው በዳሉል አካባቢ ለ24 ሰዓታት አካባቢውን ነቅቶ መጠበቅና ሠላማዊም ማድረግ የተቻለ ሲሆን፤ ከዋናው ተልዕኮ ጎን ለጎን በተካሄዱ የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠናዎች ማንኛውንም ፈተናዎች ተቋቁሞ ግዳጅን በድል መደምደም የሚችል ጠንካራ ሠራዊት መገንባት ተችሏል።

“በማያቋርጥ የዕለት ከዕለት ተልዕኮ ውስጥ ሆኖ እራስን ለቀጣይ ግዳጅ የሚያዘጋጁ ሥልጠናዎችን ማካሄድ የማይዘነጋ የግዳጅ አካል ነው” የሚሉት ዋና አዛዡ በተካሄዱ ዝግጁነትን የማረጋገጥ ሥልጠናዎች በወታደራዊ ቴክኒክ የላቀና የሥነ-ልቦና ዝግጁነቱ የተጠበቀ ሠራዊት ለመገንባት ተችሏል ብለዋል።

እንደ ብርጋዲየር ጄኔራል ሙሉ ዓለም ገለፃ ክፍለ ጦሩ በማንኛውም የግዳጅ ሁኔታ ውስጥ በድል ማለፍ የቻለ ኃይል ሆኖ ለመቀጠል የሠራዊቱ አባላት የተላበሱት ፍጹም ሀገራዊ ፍቅርና ህዝባዊ ወገንተኝነት የላቀ መሆኑ ነው በፈጠሩት ከፍተኛ ወታደራዊ አቅምና በፈጸሙት ፈታኝ ተልዕኮዎች ውጊያን ከሩቅ የማስቀረት ስትራቴጂንም ማሳካት ተችሏል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!