የዳሰሳ ጥናት እና የተሞክሮ ልውውጥ ተካሄደ

 

በባሩድ ማዕከላዊ ዕዝ በ30ኛ እግረኛ ክፍለ ጦር ውስጥ የዳሰሳ ጥናት ተካሄደ።

የማዕከላዊ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለሰው ሃብት ልማት ብርጋዲር ጄኔራል ከድር አራርሳ እና የዕዙ ከፍተኛ አመራሮች በሠራዊቱ ስነ- ልቦናዊ፣ ማህበራዊና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ጥናት አድረገዋል።

ጄኔራሉ ጥናቱን አስመልክተው በሰጡት አስተያየት ሬጅምንቱ ህዝብና መንግስት የጣለብን አደራ በድል መወጣት የሚያስችል የስነ- ልቦና አቅም እንዳለው ገልፀዋል።

የሬጅመንቱ ዋና አዛዥ ሌተና ኮሎኔል ወልዳይ ገብረ ህይወት በዳሰሳ ጥናቱ ላይ በሰጡት ማብራሪያ የሬጅመንቱ አባላት የተቋሙ ደንብ እና መመሪያ በሚያዘው መሰረት የስነ- ልቦና ግንባታ የመልካም አስተዳደር ፍትሃዊነትና የተሻለ ማህበራዊ ኑሮ ያለው መሆኑን በማብራሪያቸው ገልፀዋል።

በተያያዘ ዜና በማዕከላዊ ዕዝ የ302ኛ ሬጅመንት አባላት የተሞክሮ ልውውጥ አደረጉ።

በማዕከላዊ ዕዝ የ302ኛ ሬጅመንት ላይ በተደረገው የተሞክሮ ልውውጥ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የ30ኛ ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ ለሰው ሃብት ልማት ኮሎኔል ሙዑዝ ደስታ እንደገለፁት የግዳጅ አፈፃፀም፣ መልካም አስተዳደርና መልካም ስነ- ምግባር ለተቋሙ ተልዕኮ ስኬት የማይተካ ሚና አለው።

ከፍተኛ መኮንኑ አክለውም የሠራዊቱ መመሪያና ደንቦች፣ አሰራሮችን ቁልፍ እሴቶችን ለማስረፅና ለመላበስ የተሞክሮ ልውውጥ መድረኮች ወሳኝ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!