የሠራዊቱ አባላት ገንዘብ ለገሱ

 

በሱዳን ዳርፉር ግዳጃቸውን አጠናቀው የተመለሱ የ20ኛ ሞተራይዝድ የሠላም ማስከበር ሻለቃ የሠራዊት አባላት ለመለስ ፋውንዴሽን የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ።

የሻለቃው የሠራዊት አባላት ለመለስ ፋውንዴሽን ከእያንዳንዳቸው ሦስት ዶላር በማዋጣት በአጠቃላይ ከ64 ሺህ ብር በላይ በተወካያቸው አማካኝነት ለፋውንዴሽኑ ጽህፈት ቤት አስረክበዋል።

የ20ኛ ሞተራይዝድ ሠላም ማስከበር ሻለቃ አዛዥ ኮሎኔል ፀጋዬ ዓለማየሁ እንደተናገሩት፤ የድጋፉ ዓላማ የቀድሞ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ለታላቅ ግብና ስኬት በሚል አዎንታዊ ሃሳባቸው እና የጥበብ ተሞክሯቸውን በመጠቀም  ባበረከቱት ታሪካዊ ድንቅ ሥራቸው በስማቸው ለተቋቋመው የሳይንስና ምርምር ተቋም ለመደገፍ፣ በጎ ሥራቸውን ለትውልድ ለማስተላለፍ እና ለማስታወስ ነው ብለዋል።

ከርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ በኋላ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሪት ሰምሃል መለስ እንደገለጹት፤ የ20ኛ ሞተራይዝድ ሠላም ማስከበር ሻለቃ የሠራዊት አባላት ባደረጉት የገንዘብ ድጋፍ በፋውንዴሽኑ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!