በ25ኛ ክፍለጦር 2ኛ ሬጅመንት ቴዎድሮስ ሻምበል የምስረታ በዓሏን አከበረች

 

በ25ኛ ክፍለ ጦር 2ኛ  ሬጅመንት ቴዎድሮስ ሻምበል 1ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሏን በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት አከበረች።

በዕለቱ በክብር እንግድነት የተገኙት የክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ገብረእ ግዚአብሄር ገብረሰላም ናቸው። አዛዡ  በንግግራቸው፤ ሻምበሏ ህዝብና መንግሥት የሰጣትን ሀገራዊና ህገ-መንግሥታዊ ተልዕኮ በብቃትና በአስተማማኝ እየፈጸመች የመጣች መሆኗን በመግለጽ በቀጣይም ለበለጠ ተልዕኮ ዝግጁነትን አረጋግጦ መገኘት ይገባል ብለዋል።

የሻምበሏ ዋና አዛዥ ሻምበል ገብረስላሴ ገብረህይወት ባቀረቡት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ሻምበሏ ከተመሰረተችበት ጊዜ ጀምሮ የሠራዊቱን ሁለንተናዊ አቅም የተሻለ  ለማድረግ በተቋሙ ደንቦችና መመሪያዎች ላይ ሰፊ ውይይትና የተለያዩ ሥልጠናዎችን በማካሄድ የተሻለ አቅም በመፍጠር የተሰጣትን ግዳጅ በተሻለ ሁኔታ እየፈጸመች መሆኗን ገልጸዋል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!