ከፍተኛ ቦንድ ግዢ ለፈጸሙ የሠራዊት አባላት ዕውቅና ተሰጠ

 

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ በቦንድ ግዢ ትልቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የሠራዊት አባላት የማበረታቻ ሽልማት ተሰጠ።

በባሩድ ማዕከላዊ ዕዝ በ33ኛ ሬጅመንት ከ5 ሺህ ብር በላይ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ቦንድ ለቆረጡ ዕውቅና የተሰጠ ሲሆን፣ በዕለቱ የተገኙት የሬጅመንቷ ተወካይ አዛዥ ሌተና ኮሎኔል ዘነበ ሀመልማል እንደተናገሩት፤ ሠራዊታችን ዳር ድንበሩን ከማስጠበቅ ባሻገር የልማት አጋርነቱን እያሳየ ይገኛል። ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ዋንጫም ሬጅመንቱ ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል ብለዋል።

ከፍተኛ መኮንኑ አክለውም በዛሬው ዕለት የዕውቅና አሰጣጥ ሂደቱ በሁለት መንገድ ሲሆን በዕዝ እና በክፍለ ጦር ዕውቅና የተሰጣቸው እና በሬጅመንታችንም ደግሞ ከ5 ሺህ ብር በላይ ለአባይ ግድብ ቦንድ የገዙት የማበረታቻ ሽልማት እና ዕውቅና የመስጠት ዋና ዓላማውም በሠራዊታችን ውስጥ የእርስ በእርስ የአሀዱ እና የአይበገሬነት መንፈስ እንዲኖር ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የቦንድ ግዢ ከፈጸሙት የሬጅመንቷ አባላት መካከል ሻ/ባሻ አድማሱ አሳምነው፣ ም/!አለቃ አበበ ባራኪ በሰጡት ተመሳሳይ አስተያየት አሁን የፈጸምነው የቦንድ ግዢ እንደ ሠራዊት የሀገራችንን ሠላም ከማስጠበቅ በተጨማሪ ድህነትን ለመዋጋት በሚደረገው ርብርብ ውስጥ የልማት ሠራዊትታችን በተግባር የምናሳይበት እና የምናረጋግጥበት ነው ማለታቸውን የሬጅመንቱ ሪፖርተር ም/!አአለቃ ገብሩ መለስ ዘግቧል።

በተያያዘ ዜና በ33ኛ 1ኛ ማርታ ሬጅመንት በማዕከላዊ ዕዝና ክፍለ ጦር የተዘጋጀውን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ቦንድ ግዢን አስመልክቶ ከ5 ሺህ ብር በላይ ለገዙ የሠራዊት አባላት የምስጋና ምስክር ወረቀት ተሰጠ።

የሬጅመንቱ ምክትል አዛዥ ለሎጀስቲክ ሌተና ኮሎኔል ጀዋሮ ድኮ ዘንድሮ የታላቁ ህዳሴ ዋንጫ በሬጅመንቱ የሠራዊት አባላት ውስጥ በከፍተኛ ወኔና ተነሳሽነት ከወታደር እስከ ከፍተኛ አመራር ከወር ደመወዙ በማውጣት የበኩሉን አስተዋጽኦ አበርክቷል ብለዋል።

በዕለቱ የሽልማት ተካፋይ ከሆኑት መካከል ወ/ር ኤልሳ ጥላሁን እና ሻለቃ መጋቢ ባሻ በርሀ ኃይለሚካኤል በሰጡት አስተያየት “እኛ የሠራዊት አባላት ከተጣለብን ሀገራዊ ኃላፊነት ባሻገር በሀገር ግንባታ ላይ መሳተፋችን እጅግ የሚያስደስት ተግባር ነው” ማለታቸውን የሬጅመንቱ ሪፖርተር !አለቃ ታምሩ በኃይሉ ዘግቧል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!