ሠራዊቱ የእሳት አደጋ ተቆጣጠረ

 

በሆለታ ከተማ የሚገኘው የንጹህ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት መስሪያ ቤት ባልታወቀ ምክንያት የተነሳውን የእሳት ቃጠሎ በአካባቢው የሚገኘው ሠራዊት ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር በመሆን ተቆጣጠረ።

የሆለታ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ ገነት በየነ እንደተናገሩት፤ ጉዳት የደረሰበት የፕላስቲክ ውሃ ማስተላለፊያ ቱቦ የሆለታ ከተማን የንጹህ ውሃ መጠጥ አቅርቦት ሽፋን ለማሳደግ 45 ኪሎ ሜትር ዝርጋታ የተደረገው መሠረተ-ልማት በተቃጠለበት ጊዜ 38 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን ጠቅሰው፤ በተከሰተው አደጋም የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል።

ከንቲባዋ አያይዘውም ሠራዊታችንና ህዝባችን ባደረገው ከፍተኛ ርብርብ በሰው ህይወት ላይ ምንም ጉዳት ያልደረሰ ሲሆን፤ ወደ 100 ሚሊዮን ብር የሚቆጠር ንብረት ከእሳት ማዳን የተቻለ መሆኑን ገልጸዋል። ሠራዊቱ ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር በመሆን ሊደርስ የነበረውን ከፍተኛ ጉዳት በመከላከል ላደረገው ርብርብ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!