በልዩ ልዩ የጤና ጉዳዮች ላይ ትምህርት ተሰጠ

 

በልዩ ልዩ የሠራዊታችን  ክፍሎች የቅድመ በሽታ መከላከል የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ተሰጠ።

በማዕከላዊ ዕዝ የ8ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር 6ኛ መድፈኛ ሬጅመንት የሠራዊት አባላት የወባ በሽታን መከላከል የሚያስችል የጤና ትምህርት ተሰጠ።

በሥልጠና ሂደቱ ወቅት የሬጅመንቱ ዋና አዛዥ ተወካይ ሻምበል ጀማል ኢብራሂም እንደተናገሩት፤ ሠራዊቱ ተልዕኮውን በብቃት መወጣት የሚችለው የጤና ዝግጁነቱን አረጋግጦ ሲገኝ በመሆኑ ለጤናችን ተኩረት ሰጥተን ልንሰራ ይገባል ብለዋል።

በዕለቱ የጤና ትምህርት የሰጡት የሬጅመንቱ ጤና ዴስክ ተወካይ   አሰር አለቃ ዋጋቸው መንገሻ እንደገለጸው የወባ በሽታ አምጪ ተህዋስ በወባ ትንኝ አማካኝነት ወደ ደም ሥር በመግባት ቀይ የደም ሴልን በመውረር ለህመም የሚዳርግ በሽታ ነው። አስቀድሞ በሽታውን መከላከል እንደሚገባም ተናግረዋል።

በተመሳሳይ ዜና በማዕከላዊ ዕዝ የ33ኛ ዓባይ ክፍለ ጦር 6ኛ ሙሴ ሬጅመንት የቲቪ በሽታን የመከላከል ትምህርት ተሰጠ።

የሬጅመንቱ አዛዥ ተወካይ ሻለቃ መለሰ መኩሪያ እንደተናገሩት፤ ሠራዊታችን ካለው ማህበራዊ ኑሮ አኳያ የጤና ትምህርት መሰጠቱ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸው፤ ሠራዊታችን ለግዳጅ ዝግጁነቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የመከላከል ሥራው ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

ትምህርቱን የሰጠው  መ/% አለቃ አብራር ጀማል እንደገለጸው፤ ሠራዊታችን የተሰጠውን ታላቅ ሀገራዊ ግዳጅ ለመወጣት ጤናው የተጠበቀ መሆን እንዳለበት ጠቁመው፤ የቅደመ መከላከል ትምህርቱ አስፈላጊና ወሳኝ መሆኑን መናገራቸውን የሬጅመንቱ ሪፖርተር !አለቃ በላይ ካሳሁን ዘግቧል።

በሌላ በኩል በማዕከላዊ ዕዝ የ331ኛ ማርታ ሬጅመንት ስለ ጉበት በሽታ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ተሰጠ።

ትምህርቱን የሰጡት የሬጅመንቱ ጤና ኃላፊ ሻምበል መሰለ አሰፋ እንደተናገሩት፤ የበሽታው ዓይነት በቀጥታ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚመጣ፤ እንዲሁም በተለያዩ ስለታም ነገሮች በጋራ በመጠቀም የሚተላለፍ በመሆኑ  መላው የሠራዊቱ አባላት እራሳቸውን ከበሽታው መከላከልና መቆጣጠር እንደሚገባቸው ገልጸው፤ በሽታውን ለመከላከል በቅድሚያ ክትባት መወሰድ አስፈላጊ ነው ብለዋል። ዘገባውን ያደረሰን የሬጅመንቱ ሪፖርተር ! አለቃ ታምሩ በኃይሉ ነው።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!