አባላቱ ግዳጃቸውን በአስተማማኝ ሁኔታ እየተወጡ ይገኛሉ

 

በምዕራብ ዕዝ የ24ኛ ቴዎድሮስ ክፍለ ጦር ስር የሚገኙ የ1ኛ እና የ4ኛ ሬጅመንት የሠራዊት አባላት ግዳጃቸውን በአስተማማኝ ሁኔታ እየተወጡ  እንደሚገኙ ተገለጸ።

በ24ኛ ቴዎድሮስ ክፍለ ጦር የ4ኛ ሬጅመንት ዋና አዛዥ ሌ/ኮሎኔል ሙሀባው አበጀ እንደገለጹት የሬጅመንቱ የሠራዊት አባላት የተሰጣቸውንና የሚሰጣቸውን ተልዕኮ የሚያውቁ፤ ተልዕኮው የሚጠይቀውን ሁሉ ለመፈጸም ዝግጁነታቸውን አረጋግጠው ይገኛሉ ብለዋል።

በ24ኛ ክፍለ ጦር የ1ኛ አሉላ ሬጅመንት ምክትል አዛዥ ለአኦፕሬሽናል ሻለቃ ይስሃቅ ኤደን ኤሎ በበኩላቸው ሬጅመንቱ የተሰጠውን ማንኛውም ግዳጅ በአስተማማኝ ሁኔታ እየተወጣ መምጣቱን ገልጸዋል። ይህ ስኬት የተገኘውም በሠላም ጊዜ ዝግጁነቱን አረጋግጦ በመገኘቱ እንደሆነ ገልጸዋል።

ሬጅመንታቸው በየትኛውም ጊዜና የአየር ንብረት ግዳጃቸውን መወጣት የሚያስችል አካላዊና ሥነ- ልቦናዊ የዝግጁነት ቁመና ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!