ጄኔራል ሣሞራ የኑስ እጅግ ከፍተኛ ወታደራዊ ኒሻን ተሸለሙ

 

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ክቡር ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሆነው ሀገራቸውን በቅንነትና በታማኝነት ላገለገሉት ጄኔራል ሳሞራ የኑስ የሀገሪቱን እጅግ ከፍተኛ ወታደራዊ ኒሻን ሸለሙ ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ለክቡር ጄኔራል ሳሞራ የኑስ ሽልማቱን የሰጡት በሠራዊት ግንባታ ላስገኙት ውጤትና ላሳዩት በሳል የአመራርነት ብቃት የኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት ያላቸውን ክብር ያረጋገጡበት ደማቅ የአ ሸኛኘት ሥነ - ሥርዓት ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ.ም በብሄራዊ ቤተ- መንግሥት  በተዘጋጀበት ዕለት ነው ፡፡               

በሥነ - ሥርዓቱ ላይ ጄኔራል ሳሞራ የኑስ ላለፉት 42 ዓመታት ከተዋጊነትና አዋጊነት አንስቶ እስከ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹምነት የደረሱ ታላቅ መሪ መሆናቸውንና በስራ ዘመናቸውም የአመራርነት ብቃታቸውንና ፖለቲካዊ ብስለታቸውን ማስመስከራቸው  ተገልጿል። 

የእውቅና ፣ የሽልማትና ፣የአሸኛኘት ሥነ- ሥርዓቱ ጀኔራል ሳሞራ የኑስ የተሰጣቸውን ሀገራዊ ተልዕኮ በታላቅ ጀግንነትና ተጋድሎ በብቃት በመወጣታቸው ክብር ለመስጠት የተከናወነ መሆኑን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶክተር አብይ አህመድ ገልፀዋል ፡፡

ከኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት የተሰጣቸው ክብርና ሽልማት መላው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት አባላት  ለህገ - መንግስታዊ ሥርዓቱና ለህዝቡ ብቻ የሚያገለግሉ መሆናቸውን በተግባራዊ ሥራዎቻቸው በማረጋገጣቸው  የተሰጠ  ዕውቅና መሆኑን የተናገሩት ጄኔራል ሳሞራ የኑስ ለዚህ ታላቅ ክብር በመብቃታቸውም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

 

 

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!
በብዛት የተነበቡ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚኒስተር ለልዩ ልዩ ሞያዎች ለሚመለመሉ የመመልመያ መስፈርት አወጣ
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚኒስተር ለልዩ ልዩ ሞያዎች ለሚመለመሉ የመመልመያ መስፈርት አወጣ
 
ማሳሰቢያ
ማሳሰቢያ
የመከላከያ ኢን/ህ/ግ/ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜ/ጄኔራል መሃመድ ተሰማ በወቅታዊ ሁኔታ ላይ የሰጡት መግለጫ (የአንዳንድ ተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች የተሳሳቱ መግለጫዎችን በተመለከተ)
Video poster
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ድርጅት የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ድርጅት የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ
ኢንተርፕራይዙ ለከፍተኛ የሰራዊት እና ሲቭል አመራሮች ለስድስት ተከታታይ ቀናት የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ፡፡
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ ከተለያዪ የኣፍሪካ ሀገራት ለተውጣጡ የሠራዊት አባላት ከጃፓን መንግስትጋር በመተባበር በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ አለም አቀፍ ሰላም...