የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ት/ቤት ሰልጣኞቹን አስመረቀ

 

በሰላም ማስከበር ዋና መምሪያ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ት/ቤት አራት ሻለቃና አንድ ልዩ ልዩ ሻምበል ለሦስት ተከታታይ አሰልጥኖ አስመረቀ።

ሰሞኑን በሁርሶ ማሰልጠኛ በተካሄደው የምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ በክብር እንግድነት የተገኙ በሠላም ማስከበር ዋና መምሪያየሎጀስቲክስ ዝግጅት ስምሪት ድጋፍ መምሪያ ኃላፊ ብ/ጄኔራል ከበደ ረጋሳ ናቸው።

ጄኔራል መኮንኑ በምረቃ ስነ ስረዓቱ ላይ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር ሠራዊታችን ህዝባዊ ባህሪይ በመላበስ ባስመዘገባቸው አኩሪ የሠላም ማስከበር ግዳጅ አፈፃፀም እንዳለውና በሀገራችንም ከተልዕኮው በቀዳሚነት እንድትቀመጥ ማስቻሉ ገልፀዋል።

የዕለቱ ተመራቂዎቹ በሚሰማሩበት የሠላም ማስከበር ተልዕኮ ህዝባዊ ባህሪን በመላበስ ተልዕኳቸውን መፈፀም እንዳለባቸው ተናግረዋል።

የሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ት/ቤት አዛዥ ተወካይ ኮሎኔል ሚልኬሳ ረጋሳ ባቀረቡት የሥልጠና ሪፖርት ሠልጣኖቹን በቆይታቸው የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ህግና አሰራር እንዲሁም የግዳጅ ቀጠናዎች ባህሪና መነሻ ያደረገ ስምጠና በንድፈ ሃሳብና በተግባር በበቂ ሁኔታ መውሰዳቸው ገልፀዋል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!