ለሠላም ማረጋገጥ በጥምረት እንደሚሰሩ ምሁራን ገለፁ

 

በወለጋ  ዩንቨርሲቲ የጊምቢ ካምፓስ ምሁራን ለሀገራችንም ሆነ ለአካባቢው ሰላም በዘላቂነት መረጋገጥ በቀጠናው ካለው ኮማንድ ፖስት ጋር በጥምረት እንደሚሰሩ ገለፁ።

ምሁራኑ ይህንን የገለፁት ሰሞኑን በምዕራብ ወለጋ ዞን ከተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ጋር ስለአስቸካይ ጊዜ አዋጁ አስፈላጊነት፤ አተገባበርና ወደፊት ከባለድርሻ አካላት ስለሚጠበቀው ተግባራት በተወያዩበት ወቅት በሰጡት አስተያየት ነው።

“የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ድርሻ በራሱ የሚተማመን፤ የበቃ ሀገር ተረካቢ ዜጋ ማፍራት መሆኑን” ያወሱት ምሁራኑ “ይሄን ታላቅ ሃላፊነት ማሳካት የሚቻለው ሠላም ሲኖር በመሆኑ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ አግባብ ነው፤ ለተግባራዊነቱም የበኩላችንን ሃላፊነት እንወጣለን” ብለዋል።

በዞኑ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ኮሎኔል ተስፋዬ ነጋሽ በበኩላቸው፤ “በመማር ማስተማር ሂደት መልካም ስም ያለው የወለጋ ዩንቨርስቲ ጊምቢ ካምፓስ መምህራን ያነሱት ሀሳብ ትክክለኛና ወቅታዊ መሆኑን ጠቁመው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ከሰሩ የሀገራችንን ዘላቂ ሰላም ሁሉን ተጠቃሚ ማድረግ የሚችል ልማት ማስቀጠል እንደሚችል አመልክተዋል”።

“ከሠላሙ ትሩፋቶች አንዱ ለበርካታ ኢትጵያውያን የዕውቀት ስንቅ በማስታጠቅ ላይ የሚገኘው የጊምቢ ካምፓስ አንዱ መሆኑን” የገለጹት ኮሎኔል ተስፋዬ፤ “ከዚህም የበለጠ ዕድገት ማምጣት የሚቻለው አስተማማኝ ሰላም ሲረጋገጥ በመሆኑ ምሁራኑ ሃላፊነታቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል” ብለዋል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!
በብዛት የተነበቡ የክቡር የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን የህይወት ታሪክ
የክቡር የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን የህይወት ታሪክ
ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ከአባታቸው ከ፲አለቃ መኮንን ይመር አና ከእናታቸው  ከወ/ሮ ሂይወት ይህደጎ ተላ በትግራይ ክልል በሰሜን ምዕራብ ዞን አስገደ ምጽብላ...
ፋውንዴሽኑ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች ሊያስረክብ ነው
ፋውንዴሽኑ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች ሊያስረክብ ነው
የመከላከያ  ፋውንዴሽን  በመጀመሪያ ዙር ያስገነባቸውን 112 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በቅርቡ ለሠራዊቱ በዕጣ ለማስተላለፍ ዝግጅት መጠናቀቁን የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ዋና ስራ...
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ውጤታማ ስራ ማከናወኑ ተገለጸ
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ውጤታማ ስራ ማከናወኑ ተገለጸ
የመከላከያ ኮንስተራክሽን ኢንተርፕራይዝ  በ2011 የበጀት አመት በርካታ ዉጤታማ ስራዎች ማከናወኑ ተገልጿል፡፡
ኮሌጁ ሶስተኛውን ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ አካሄደ
ኮሌጁ ሶስተኛውን ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ አካሄደ
የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ሦስተኛውን ሀገርአቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ አካሄደ።
ሰኔ 14 10 2011 መከላከያ ሬዲዮ ዜና