ከተለያዩ ክፍሎች ለተውጣጡ አመራሮችና ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ

 

በሰላም ማስከበር ስልጠና ማዕከልና በጃፓን ኤምባሲ ትብብር የተዘጋጀ የሰልጥኖ አሰልጣኞች ስልጠና ከተለያዩ ክፍሎች ለተውጣጡ የግዳጅ ስምሪት ባለሙያዎችና አመራሮች አዲስ አበባ በሚገኘው የሰላም ማስከበር ስልጠና ዋና ቢሮ ተሰጠ።

ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የሰላም ማስከበር ማሰልጠኛው አዛዥ ብ/ጄ ሀብታሙ ጥላሁን “ሀገራችን በአሁኑ ወቅት በተባበሩት መንግስታትና በአፍሪካ ህብረት ስር በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ላይ ከአስራሶስት ሺ በላይ ወታደሮችን በማሰማራት ከአለማችን ቀዳሚ መሆኗን” ጠቁመዋል።

“ስልጠናው ለሰልጣኞች የተሻለ አቅም እንደሚፈጥርና በሰላም ማስከበር የግዳጅ ስምሪት ላይ ማሰልጠኛው ከተለያዩ አጋር ሀገራት ጋር በጋራ እየሰራ እንደሚገኝ” ያወሱት ጄኔራል መኮንኑ “የጃፓን ኤምባሲ ስልጠናውን በገንዘብ በመደገፉ ምስጋናቸውን” አቅርበዋል።

“ሰልጣኞች ከስልጠናው ያገኙትን አቅም በመያዝ ለአባላቶቻቸው በማሰልጠንና በተግባር ላይ በማዋል የሀገራችንን የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ውጤታማ እንዲሆን የበኩላቸውን እንዲወጡም” አሳስበዋል።

በሰላም ማስከበር ማሰልጠኛው ማዕከል የፀጥታና ደህንነት ስልጠና ዲፓርትመንት ሃላፊ አቶ ዳዊት አሰፋ “ስልጠናው በሰላም ማስከበር የግዳጅ ስምሪትን በተሻለ ሁኔታ ለመፈጸም ያግዛል” ብለዋል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!
በብዛት የተነበቡ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚኒስተር ለልዩ ልዩ ሞያዎች ለሚመለመሉ የመመልመያ መስፈርት አወጣ
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚኒስተር ለልዩ ልዩ ሞያዎች ለሚመለመሉ የመመልመያ መስፈርት አወጣ
 
ማሳሰቢያ
ማሳሰቢያ
የመከላከያ ኢን/ህ/ግ/ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜ/ጄኔራል መሃመድ ተሰማ በወቅታዊ ሁኔታ ላይ የሰጡት መግለጫ (የአንዳንድ ተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች የተሳሳቱ መግለጫዎችን በተመለከተ)
Video poster
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ድርጅት የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ድርጅት የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ
ኢንተርፕራይዙ ለከፍተኛ የሰራዊት እና ሲቭል አመራሮች ለስድስት ተከታታይ ቀናት የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ፡፡
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ ከተለያዪ የኣፍሪካ ሀገራት ለተውጣጡ የሠራዊት አባላት ከጃፓን መንግስትጋር በመተባበር በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ አለም አቀፍ ሰላም...