“ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ህገወጥ በሆነ እንቅስቃሴ ማፍረስና ስልጣን በአቋራጭ መያዝ አይቻልም!!” አቶ ሲራጅ ፈጌሳ

 

“ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ህገወጥ በሆነ እንቅስቃሴ ማፍረስና ስልጣን በአቋራጭ መያዝ አይቻልም!!”  አቶ ሲራጅ ፈጌሳ

“ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ህገወጥ በሆነ እንቅስቃሴ ማፍረስና ስልጣን በአቋራጭ መያዝ አይቻልም!!” ሲሉ የመከላከያ ሚንስቴርና የኮማንድፖስት ሴክሬቴሪያት አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ገለጹ፡፡

የመከላከያ ሚንስቴርና የኮማንድ ፖስት ሴክሬቴሪያት አቶ ሲራጅ ፈጌሳ በወቅታዊ የሀገራችን ጉዳይ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ “በሀገራችን በአሁኑ ወቅት የተጠናከረ የመንግስት ስርዓት መኖሩና በህዝቡ የተነሱትን ትክክለኛ ጥያቄዎችን በመቀልበስ በህገወጥ መልኩ የመንግስትን ስልጣን መያዝ እንደማይቻል” ገልጸዋል።

“ህዝቡ ያነሳቸውን ትክክለኛ የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎች ይዘቱን በመለወጥ በተለይም በማህበራዊ ሚዲያዎች በመቀስቀስ ወጣቱን ወዳላወቀው እንቅስቃሴ የሚከቱ የነውጥ ሀይሎች የሞት ሽረት እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆናቸውን” ጠቁመዋል።

“የነውጥ ሀይሎቹ ፍላጎት በሀገሪቱ የህግ የበላይነት እንዳይከበርና መንግስት ከህዝቡ ጋር በመሆን እየሰራቸው ያሉትን ስራዎች ተግባራዊ እንዳይሆኑ ለማድረግ ያለመ” መሆኑን የገለጹት ሚንስቴሩ “የደሀ ዜጎችን ህይወት በማመሰቃቀል ወደ ስልጣን መምጣት አይቻልም” ብለዋል።

“የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሳይታወጅና ከታወጀም በኃላ ተግባራዊ እንዳይሆን የተለያዩ የውጭ ሀይሎችና የሀገር ውስጥ ፀረ ሰላም ሀይሎች ከፍተኛ ቅስቀሳ ቢያደርጉም አዋጁ በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነትን አግኝቷል” ብለዋል።

“የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ህዝቡ ህጋዊ በሆነ መልኩ መብቱ እንዲከበርለትና የፀጥታ አካላትም ስራቸውን በተገቢው መንገድ እንዲያከናውኑ እየረዳ መሆኑንም” ጠቅሰዋል።

“የነውጥ ሀይሎች በተደራጀ የነውጥ እንቅስቃሴ የፀጥታ ሀይሎችን መተናኮሳቸውን በአስራሰባት የፀጥታ ሀይሎች ላይ የመቁሰል አደጋ ቢደርስም ህዝባዊ ውግንናቸውን በሚያሳይ መልኩ መስዋዕትነት እየከፈሉ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት እየጣሩ ለሚገኙት ለፀጥታ አካላት ለአካባቢ መስተዳደሮችና ለህዝቡ ምስጋና አቅርበዋል”።

“ከኃላ ያለውን ድብቅ አጀንዳ የማይረዱ በርካታ ንፁሀን ዜጎች በነውጡ ተሳታፊ መሆናቸውን” የገለፁት ሚንስቴሩ “መንግስት በታላቅ ትዕግስት ነገሮችን ለማስተካከል እየጣረ መሆኑና በነውጡ ዋነኛ ተሳታፊ የሆኑትን በመለየት ህጋዊ እርምጃ መውሰዱን እንደሚቀጥልም” አሳስበዋል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!