አዲሱ ትውልድ የአድዋ ድል ትሩፋቶችን አጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠየቀ

 

አዲሱ ትውልድ የአድዋ ድል ትሩፋቶችን አጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠየቀ

 

የሀይማኖት አባቶችና የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች “ወጣቱ ትውልድ በህብረት በመቆም አባቶቹ ያቆዩለትን ታሪክ ድህነትን በማሸነፍ ሊወጣ እንደሚገባ” አሳሰቡ።

ይህን ያሳሰቡት በአዲስ አበባ ኮምንኬሽን ጉዳዮች ቢሮና በአፍሪካ ቤዛ ኮሌጅ አዘጋጅነት “አድዋ የአብሮነትና የአሸናፊነት ተምሳሌት ነው” በሚል መሪ ቃል ለ122ኛ ጊዜ የአድዋ ድል በዓል የከተማው አስተዳደር አመራሮች፤  ከጀግኖች አርበኞች ፤ከሀይማኖት አባቶች፤ ከመከላከያ ሰራዊት አባላትና ከከተማው ነዋሪዎች ጋር በመሆን በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት በደማቅ ሁኔታ ባከበሩበት ወቅት ነው።

በበዓሉ ላይ የተገኙት የከተማው አስተዳደር ምክርቤት አፈጉባኤ አቶ ታቦር ገብረመድህን “ወጣቱ ትውልድ ድህነትን በማሸነፍ የአባቶቹን ታሪክ ጠብቆ ሊቆይ ይገባል” ብለዋል።

“የአድዋ ድል ለፓን አፍሪካ እንቅስቃሴ ያደረገው አስተዋፅኦ” እና “ባህልና የቋንቋ እሴቶቻችን ለአድዋ ድል የነበራቸው አስተዋፅኦ” እንዲሁም “ሰውና ሀገር” በሚሉ ርዕሶች የተለያዩ ምሁራን ጥናታዊ ፅሁፎችን በማቅረብ አወያይተዋል።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ፅህፈት ቤት የሚዲያና ኮምንኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሀይሉ አብርሀ ግድቡ የደረሰበትን ደረጃ ያብራሩ ሲሆን “ግድቡ በታቀደለት ጊዜ እየተካሄደ” መሆኑን ገልጸዋል።

የመከላከያ ኢንጅነሪንግና ኮርፖሬሽን ተወካይ ሻምበል ይኩኖአምላክ ተስፋይ ኮርፖሬሽኑ የደረሰበትን የእድገት ደረጃና እየሰራ ያለውን ስራዎች ለታዳሚያን አቅርበዋል።

በበዓሉ ላይ ወጣቶች ከጀግኖች አባት አርበኞች የባንዲራ ርክክብ ያደረጉ ሲሆን የአድዋ ድል በዓልን የሚዘክር ሙዚቃዊ ድራማም በዝግጅቱ ላይ ቀርቧል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!
በብዛት የተነበቡ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ በጀኔራሎቹ ሹመት ስነ-ስርዓት ላይ ያስተላለፉት መልዕክት
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ በጀኔራሎቹ ሹመት ስነ-ስርዓት ላይ ያስተላለፉት መልዕክት
ኢትዮጵያውያን ሁሉ በተፈጥሮ ወታደሮች ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ወታደሮች ደግሞ የተፈጥሮ ወታደርነትን ከዘመናዊ ስልጠናና ከዲስፕሊን ጋር ያዋሀዱ ምርጦች ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ ይህ ነው...
ታህሳስ 26 04 2012 መከላከያ ቴሌቪዥን ዜና
Video poster
በሰው ኃብት ልማት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
በሰው ኃብት ልማት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ አየር ኃይል ደረጃ ለመምሪያ ኃላፊዎች እና ለሰው ኃብት ልማት ሙያተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡ ከመከላከያ ሰው ሀብት ዋና መምሪያ...
ጥር 03 05 2012 መከላከያ ቴሌቪዥን ዜና
Video poster
የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ የሴቶች ጉዳይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት አካሄደ
የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ የሴቶች ጉዳይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት አካሄደ
የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ የሴቶች ጉዳይ በጦር ሃይሎች ከምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመገኘት የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት አካሄደ፡፡