ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ሴክሬታሪያት ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ

 

ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ሴክሬታሪያት ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ

 በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠረውን የፀጥታ መደፍረስ ችግር ለመቆጠጠር በቅርቡ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ በመንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንደደነገገ ያስታወሰው የኮማንድ ፖስቱ መግለጫ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከወጣ ወዲህ የፀጥታ ሀይሎች ባደረጉት ፈጣን እንቅስቃሴ እና ሰላሙ ታውኮ በቆየው ህዝብ የነቃ ተሳትፎ እና ትብብር ከሞላ ጎደል በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ የተረጋጋ ሰላማዊ ሁኔታ ለመፍጠር ተችሏል ብሏል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀ በኋላ በአብዛኛው የሃገሪቱ አካባቢ ሰላምና መረጋጋት እየተፈጠረ የመጣ ቢሆንም ባለፉት ሁለትና ሶስት ቀናት በኦሮሚያ አካባቢ በተለይ በነቀምቴ እና ደምቢዶሎ ከተሞች የህዝቡን ሰላምና መረጋጋት ለማደፍረስ ጥረት ከማድረግ ባሻገር በፀጥታ ሀይሎች ላይ የእጅ ቦምብ በመወርወር አደጋ ለማድረስ እንቅስቃሴ መደረጉን ጠቅሷል፡፡

የፀጥታ ሀይሎች ሰላምና መጋጋት ለረጋገጥ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ በተቻለ መጠን የሰው ህይወት እንዳይጠፋ አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲያደርጉ በተሰጣቸው መመሪያ መሰረት እየቸገሩና አልፎ ተርፎም ራሳቸውንም ለአደጋ እያጋለጡ ሁኔታውን በቁጥጥር ስር ለማዋል ትእግስት በተሞላት ሁኔታ አስፈላውን ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውንም አስታውቋል፡፡

ይሁን እንጂ እነዚህ ሀይሎች ከዚህ የጥፋት ድርጊታቸው በአፋጣኝ የማይቆጠቡ ከሆነ በስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመመሪያው መሰረት በእነዚህ አካላት ላይ አስፈላጊው እርምጃ ሁሉ እንዲወስዱ ለፀጥታ ሀይሎቻችን ትእዛዝ መሰጠቱን ገልጿል፡፡

ከዚህ ሌላ በኦሮሚያ ክልል የህዝብ ተወካዮች አባላት የመኖሪያ ቤትና አድራሻ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች በማሰራጨት ፀረ-ሰላም ሀይሎች በአካል እቤታቸው ድረስ በመሄድና ስልክም በመደወል እያስፈራሩዋቸው መሆኑን የህዝብ ተመራጮቹ ራሳቸውና ቤተሰቦቻቸው ለኮማንድ ፖስቱ ተደጋጋሚ አቤቱታ በቅረብ ላይ ናቸው ብሏል፡፡

ይህ ፀረ ዴሞክራሲያዊ አካሄድና ፍላጎትን በሀይል ለመጫን የሚደረግ አፍራሽ እንቅስቃሴ ኮማንድ ፖስቱ በቸልታ እንደማይመለከተውና በዚህ ተግባር ላይ በተሰማሩ ሃይሎች ላይ አስፈላጊ ክትትል በማድግ ህጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን በጥብቅ አስጠንቅቋል፡፡

በተለያዩ የሃገራችን አካባቢዎች የሚገኘው ህዝባችን የራሱን ህይወትና ንብረት ከጥቃት ለመጠበቅ ከፀጥታ ሀይሎቻችን ጎን ተሰልፎ መስዋእትነት ጭምር እየከፈለ ለኮማንድ ፖስቱና ለፀጥታ ሃይሎች እየሰጠ ላለው ድጋፍ የኮማንድ ፖስቱ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ምስጋና አቅርቧል፡፡
የሀገሪቱ ሰላም ሙሉ ለሙሉ ለማረጋገጥ መንግስትና የፀጥታ ሀይሎች የሚያደርጉት ጥረት እንዲሳካ ህዝቡ የጀመረውን ሁለ ገብ ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጽህፈት ቤቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!