ለኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ሰራዊት የሜዳልያ ሽልማት ተበረከተ

ለኢትዮጵያ  የሰላም  አስከባሪ ሰራዊት የሜዳልያ ሽልማት ተበረከተ፡፡

 

በተባበሩት መንግስታት  በአቢዬ  በሰላም ማስከበር ግዳጅ ላይ ለተሰማራው የኢትዮጵያ 17ኛው የሰላም ማስከበር ሞተራይዝ ድሻለቃ በቀጠናው ላስመዘገበው የሰላም ማስፈንና የፀጥታ ማረጋገጥ እንቅስቃሴ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሜዳልያ ሽልማት ተበረከተለት።

በአብዬ  ዲፍራ አካባቢ ለሚገኘው የ17ኛው ሞተራይዝድ ሻለቃ ሽልማቱ የተበረከተለት የግዳጅ ቀጠናው ከጦር መሳሪያ ነጻ እንዲሆን ፤ የአካባቢውን ነዋሪዎችን ደህንነት በመጠበቅ፤ የሰብሀዊና የእርዳታ ድርጅቶችን ፤ የተባበሩት መንግስታት ሲቭል ሰራተኞችንና ንብረቶችን ከአደጋ ለመከላከል የተሰጠውን ግዳጅ በከፍተኛ ሀላፊነትና ውጤታማነት ማከናወን በመቻሉ ነው።

የሜዳልያ ሽልማቱ የሚሰጠው በተባበሩት መንግስታት ሰላም ማስበር ግዳጅ ላይ ለሚሰማሩ ወታደሮች በሚያስመዘግቡት ከፍተኛ ውጤት ነው።

በሜዳሊያ አሰጣጥ ስነስርዓቱ ላይ በተባበሩት መንግስታት ሰላም ማስከበር በአቢዬ የዩኒስፋ ሃይል አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ተስፋይ ግደይና ሌሎችም ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮችና የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎችም በመገኘት ለሰራዊታችን ያላቸውን ክብር ገልጸዋል።

 

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!