የኢፌዴሪ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ጄኔራል ሳሞራ የኑስ መልዕክት!

                       በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ!

                         ዘላለማዊ ክብር ለጀግኖች ሰማዕታት!

የኢፌዴሪ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታ ማዦር  ሹም ጄኔራል ሳሞራ የኑስ መልዕክት!

 

በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ የሠላም ማስከበር ተልዕኮ አኩሪ ግዳጅ በመፈጸም ላይ የምትገኙ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን አባላትና መላው ሲቪል ሠራተኞች እንኳን ለ6ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን አደረሳችሁ!!

ውድ የመከላከያ ሠራዊታችን አባላት!

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የሀገራችን ብሄር፡ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ተስማምተው ባጸደቁት ህገ-መንግሥታቸው አማካኝነት ህገ-መንግሥታዊ ተልዕኮ ሰጥተውታል። ሠራዊታችን የሀገራችን ህዝቦች የሰጡትን ተልዕኮ በብቃት ለመፈጸምም የሚያስችሉትን ብቃቶች እንዲላበስ ባለፉት ዓመታት በርካታ ሥራዎች ተሰርተዋል።

ሠራዊታችን የተሰጡትን ተልዕኮዎች በብቃት መፈጸም እንዲችል፣ ዘመናዊና ፕሮፌሽናል ሠራዊት እንዲሆን የሚያስችሉና ሁለንተናዊ አቅሙን የሚያሳድጉ የአቅም ግንባታ ሥራዎች በስፋት ተከናውነዋል።

ተቋማችን ህገ-መንግሥታዊ ተልዕኮውን በብቃት መፈጸም የሚያስችሉትንም አደረጃጀቶች በየጊዜው እያጠናከረ የሠራዊቱን የመፈጸም አቅም የሚያሳድጉ ሥራዎችን በመስራት ዛሬ ሠራዊታችን በአንዴ በርካታ ግዳጆችን መፈጸም የሚችል ሠራዊት ሆኗል።

ተቋማችን ሠራዊቱ የዘመናዊና ፕሮፌሽናል ሠራዊት አሠራር እንዲኖረው የሚያስችሉ በርካታ ደንብና መመሪያዎችን ቀርጾ ተግባራዊ አድርጓል። በዚህም ሠራዊታችን ሁሉንም ሥራዎቹን የሚያከናውነውና የሚመራው በደንብና በመመሪያዎች ሲሆን፤ ዴሞክራሲያዊ አመራርና አሰራር ያለው ሠራዊትም እንዲሆን አስችሎታል።

ጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን አባላት!

ሠራዊታችን ግዳጁን በአግባቡ እንዲፈጽምና ውጤታማ የግዳጅ አፈጻጸም እንዲኖረው በሁሉም ዘርፍ ብቃት እንዲላበስ በትምህርትና ሥልጠና ተቋሞች እራሱን እያጎለበተ ይገኛል። በተለያዩ የአቅም ግንባታ ሥራዎች በተላበሳቸው አቅሞች በአንድ ጊዜ (በተመሳሳይ) የሚሰጡትን የተለያዩ ግዳጆች መፈጸም የሚችል ሠራዊት መገንባት ተችሏል። በዚህ የመፈጸም ብቃቱም በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የተሰጡትን ተልዕኮዎች በብቃት ማሳካት ችሏል። በዚህ ተግባሩም የኢትዮጵያ ህዝቦች የሚመኩበትና የሚተማመኑበት ሠራዊት ተገንብቶ ማየት ችለዋል።

የተከበራችሁ የመከላከያ ሠራዊታችን አባላትና ሲቪል ሠራተኞች!

ሠራዊታችን ከኤርትራ መንግሥት  የተቃጣብንን ወረራ በመቀልበስ ዳግም የወረራ ሙከራ እንዳይደረግ ጦርነትን የመግታት ግዳጅ በተሟላ በመፈጸም አስተማማኝ የሠላም ኃይል መሆኑን አስመስክሯል። በአሁኑ ወቅትም  የህዝብ ሉዓላዊነትን በማስጠበቅ አኩሪ ግዳጅ እያስመዘገበ ይገኛል።

በሀገር ውስጥ ፀረ-ሠላምና ፀረ-ልማት ኃይሎች ሁከት በማስነሳት በአመጽና በኃይል ህገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለማፍረስ  የሚፈጽሙትን እኩይ ተግባርም ሠራዊታችን ለማናቸውም ችግሮች ሳይበገር የተሰጠውን የግዳጅ አፈጻጸም መመሪያና ህጎች በብቃት በመተግበር ግዳጁን እየተወጣ መጥቷል። ይህ አኩሪ ተግባሩንም አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።

ሠራዊታችን በአህጉራዊና ዓለምአቀፋዊ የሠላም ማስከበር ተልዕኮ በስፋት እየተሳተፈ ይገኛል። በተልዕኮዎቹም ውጤታማ ከመሆን አልፎ ቀዳሚ ተሰላፊ መሆን ችሏል። ተመራጭ የሠላም ኃይልም ሆኗል። ሠራዊታችን በሠላም ማስከበር ተልዕኮ እየተወጣ ያለውን ስኬታማ ግዳጅም ይበልጥ አጠናክሮ ይቀጥላል።

ጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን!

በመጨረሻም የማስተላልፈው መልዕክት፣ ሠራዊታችን በቀጣይ ተልዕኮዎቹን በውጤታማነት እንደሚፈጽማቸው ሙሉ እምነት አለኝ።

የሠራዊት ፕሮፌሽናልነት በአንድ ወቅት የሚፈጸም ተግባር አይደለም። በመሆኑም በየደረጃው ያሉ የሠራዊቱ አመራሮችና አባላት በተቋማችን የወጡትን ደንቦች፣ መመሪያዎችና አሠራሮችን በተሟላ ሁኔታ መተግበር ይኖርባቸዋል። በዚህም የሠራዊቱን ፕሮፌሽናልነት የመገንባት ጥረቱ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።

ሠራዊታችን በሀገር ውስጥ የተፈጠረውን ሁከትና ብጥብጥን የማስቆምና ሀገርና ህዝብን የማረጋጋት ወቅታዊ ህገ-መንግሥታዊ ተልዕኮውን የፈጸመበትን ፍጹም ህዝባዊ ባህሪይ ጠብቆ ማስቀጠል ይኖርበታል።

ዴሞክራሲያዊ አሠራርን በውጤታማነት በመተግበር እንዲሁም ጓዳዊ ግንኙነትን በማጠናከር፤ የሠራዊቱን አኗኗር የማሻሻል ጥረትን በማፋጠን የተሰጠንና የሚሰጠንን ግዳጆች በብቃት መፈጸም ይኖርብናል።

                                  ዘላለማዊ ክብር ለጀግኖች ሰማዕታት!

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!
በብዛት የተነበቡ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚኒስተር ለልዩ ልዩ ሞያዎች ለሚመለመሉ የመመልመያ መስፈርት አወጣ
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚኒስተር ለልዩ ልዩ ሞያዎች ለሚመለመሉ የመመልመያ መስፈርት አወጣ
 
ማሳሰቢያ
ማሳሰቢያ
የመከላከያ ኢን/ህ/ግ/ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜ/ጄኔራል መሃመድ ተሰማ በወቅታዊ ሁኔታ ላይ የሰጡት መግለጫ (የአንዳንድ ተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች የተሳሳቱ መግለጫዎችን በተመለከተ)
Video poster
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ድርጅት የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ድርጅት የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ
ኢንተርፕራይዙ ለከፍተኛ የሰራዊት እና ሲቭል አመራሮች ለስድስት ተከታታይ ቀናት የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ፡፡
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ ከተለያዪ የኣፍሪካ ሀገራት ለተውጣጡ የሠራዊት አባላት ከጃፓን መንግስትጋር በመተባበር በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ አለም አቀፍ ሰላም...