የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ክቡር አቶ ሲራጅ ፈጌሳ መልዕክት!

የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ክቡር አቶ ሲራጅ ፈጌሳ መልዕክት!

 

የተከበራችሁ መላው የመከላከያ ሠራዊት አባላትና ሲቪል ሠራተኞች እንኳን ለ6ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን አደረሳችሁ፤ አደረሰን!!

የተከበራችሁ የሠራዊት አባላትና ሲቪል ሠራተኞች!

የመከላከያ ሠራዊታችንን ቀን የካቲት 7 በአዋጅ በተፈቀደው መሠረት በያዝነው የ2010 ዓ.ም ህዝባዊ ባህሪያችንን እያጎለበትን ህገ- መንግሥታዊ ሥርዓታችንን በመጠበቅ የሀገራችን ህዳሴ ዋስትና ሆነን እንቀጥላለን በሚል መሪ ቃል ለ6ኛ ጊዜ ከህዝባችን ጋር እናከብረዋለን። ይህን ቀን ላለፉት አምስት ተከታታይ ዓመታት ከመንግሥታችን እና ከህዝባችን ጋር ሆነን በማክበራችን ከፍ ያለ ጠቀሜታ እንዳለው አረጋግጠንበታል። በመሆኑም የመከላከያ ሠራዊታችን ህገ-መንግሥታዊ ዕምነቱን፣ ህዝባዊነቱንና ወታደራዊ ዝግጁነቱን በማጠናከር የሀገራችን ሠላም ዘላቂና አስተማማኝ እንዲሆን ያበረከተውን እና እያበረከተ ያለውን የዜግነት አስተዋጽኦ በአግባቡ ለማስተዋወቅ አግዞናል። ይህን ተልዕኮውን በፅናት በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ በማሳካት ሂደት የከፈለው መስዋዕትነት ክብር እንዲሰጠውም ቀኑ መታሰቡ መልካም መድረክ ሆኗል። በአጠቃላይ ይህን ቀን ከህዝባችንና ከወዳጆቻችን ጋር ሆነን ማሰባችን የመከላከያ ሠራዊታችን በጥቅሉ ደግሞ የተቋማችን ገጽታ በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲጎላ አድርጓል።

ጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን!

ይህን ዕለት ዘንድሮም ለ6ኛ ጊዜ ማክበራችን የገጽታ ግንባታ ሥራችንን የበለጠ ያጠናክራል። ስለሆነም ቀኑን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ከህዝባችን ጋር ስናከብረው ሠራዊታችን አሁንም ሆነ ለወደፊት ቁርጠኛ የሠላምና የልማት ኃይል መሆኑን አጉልተን ማሳየት ይኖርብናል። በተለይም ሠራዊታችን ባለፉት ዓመታት ህዝባዊነቱን የበለጠ በማጠናከር ሠላማችንን ለማስፋፋት የላቀ ሚና ተጫውቷል። በአንዳንድ የሀገራችን ክልሎች ተከስቶ የነበረውን ሁከትና አለመረጋጋት ከአካባቢው ህዝብ፣ የመስተዳድር አካላትና የፀጥታ ኃይሎች ጋር በመቆጣጠር ሠላማችን ወደነበረበት እንዲመለስ ጉልህና መተኪያ የሌለው ድርሻ አበርክቷል። እንዲሁም ሠራዊታችን ህዝቡ ዋነኛ የሠላም ኃይል መሆኑን በመገንዘብ ከህዝብ ጋር በመስራት የፀረ-ሠላም ኃይሎችን ምኞት አምክኗል። ሠላማችን ዘላቂና አስተማማኝ እንዲሆን በማስቻሉም መንግሥት የህዝብን ጥያቄዎች በተረጋጋ ሥርዓት ለመመለስ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮለታል። ይህም በጋራ ድህነትን ለማስወገድ የጀመርነውን ሀገራዊ ትግል ወደፊት እያራመደው ነው።

ውድ የመከላከያ ሠራዊታችንና ሲቪል ሠራተኞች!

ሠላማችንን ባለፉት ዓመታት በከፍተኛ ትግልና መስዋዕትነት ነው ያረጋገጥነው። ውጤቱም የሚያኮራ ነው። የዕድገትና ብልፅግና ጉዟችን ተጠናክሯል። ለወደፊትም ቢሆን ሠላማችን እየጎመራ ልማታችን የህዝብን ፍላጎትና ግብ እያሳካ በሄደ ቁጥር ከውስጥም ከውጭም ፈተናዎች መበርከታቸው አይቀርም። በቀላሉ አነጋገር ሠላማችንን ለመንጠቅ የሚሹ ኃይሎች ፍላጎትና ተግባራዊ እንቅስቃሴ ሊጠናከር እንደሚችል መገመትይችላል።

ስለሆነም 6ኛውን የመከላከያ ሠራዊት ቀን ከህዝባችን ጋር ስናከብር የሠላም ቁርጠኝነታችንን ማረጋገጥ አለብን። ሁለንተናዊ ዝግጁነታችን የሠላምና የልማት መሠረታዊ አቅሞች መሆናቸውን በአግባቡ ማሳወቅም ይጠበቅብናል። ህዝባችን ቀዳሚው የሠራዊታችን የጥንካሬ ምንጭ እንደሆነም ያለፉት ዓመታትን ተሞክሮዎች ያስረዳሉ። ስለዚህ ዕለቱን በጋራ ስናከብር ላለፉት አምስት ዓመታት በሠራዊቱ ቀን አከባበር የተገኙ ተሞክሮዎችን በመቀመር ትምህርት በማስተላለፍ መሆን አለበት። ይህን የሠራዊት ቀን ስናከብርም የተለያዩ የህዝብ አካላትን ገንቢ አስተሳሰቦች በመተንተን ግዳጃችንን በሚያጠናክር መልኩ ልንጠቀምበት ይገባል።

ውድ የሠራዊታችን አባላት!

የሠራዊቱን አኗኗር ምቹና ዘመናዊ እንዲሆን የሠራዊቱን ሙያዊ አቅም በማሳተፍ ጭምር ጥረቶች ተጠናክረዋል። ውጤቱም ለተጨማሪ ሥራ የሚያነሳሳ ሆኗል። ስለዚህ የሠላም አስተዋጽኦችን ወሳኝ በመሆኑ ግዳጃችንን ሳይንሳዊና ዘመናዊ በማድረግ አመራሩና ሠራዊቱ የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!