ሠራዊቱ ወደ ክልሎች የገባው በህጉ መሠረት ጥያቄ ቀርቦለት ነው
-ክቡር አቶ ሲራጅ ፈጌሳ የመከላከያ ሚኒስትር
መከላከያ ለማረጋጋት ወደ ክልሎች የገባው በህገ- መንግሥቱ መሠረት ጥያቄ ቀርቦለት መሆኑን ሚኒስትሩ ክቡር አቶ ሲራጅ ፈጌሣ አመለከቱ።
ሚኒስትሩ ይሄንን ያመለከቱት ሰሞኑን በኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች መኮንኖች ክበብ የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤትን የሁለት ወራት ግምገማ አስመልከቶ ለሀገር ውስጥ ጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው።
ተቋሙ ህገ- መንግሥቱን ተከትሎ በመመሪያና አመራር ብቻ ተግባራቱን እንደሚያከናውን የገለፁት ሚኒስትሩ፤ በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች ተከስቶ የነበረውንም አለመረጋጋት ከሠላም ወዳዱ ህዝብና የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር ማረጋጋት መቻሉን አመልከተዋል።
ዜና በፈይሣ ናኔቻ (ሻምበል) Jan 12, 2018 654 ጊዜ ተነበዋል
ጥር 21 05 2011 መከላከያ ሬዲዮ ዜና |
ጥር 17 05 2011 መከላከያ ሬዲዮ ዜና |