በብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን የተሰሩ ዘመናዊ ተደራራቢ አውቶብስና የተማሪ ሰርቪሶች ርክክብ ተካሄደ።

የመከላከያ ብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን አካል የሆነው የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ የሰራቸውን  ዘመናዊ ተደራራቢ አውቶብስና የተማሪ ሰርቪሶች ለአዲስ አበባ መስተዳደር ህዳር 23-2010 ዓ/ም አስረከበ።

በርክክብ ስነ ስርሀቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከንቲባ ክቡር አቶ ዲሪባ ኩማ በከተማዋ የሚታየውን የትራንስፖርት እጥረት ለማቃለል አስተዳደሩ ከ3 ነጥብ አራት ቢሊየን ብር በላይ በማውጣት 850 የብዙሀን ተሽከርካሪዎች ከብረታ ብረትና እንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን   መግዛቱን ገልጸዋል

ሜቴክ ዘመናዊና ደረጃቸውን የጠበቁ ብዙሀን ተሽከርካሪዎችን ከማምረቱም በላይ የሀገሪቱን የኢንዱስትሪ እድገት እያሻሻለ እንደሚገኝ የጠቆሙት ከንቲባው በውሉ መሰረት በጊዜው አጠናቆ ላስረከባቸው ተሽከርካሪዎች በአስተዳደሩና በከተማው ነዋሪዎች ስም ለኮርፖሬሽኑ ምስጋና አቅርበዋል

የብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ም/ል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ብ/ጄ ጠና ቁሩንዲ እንደገለጹት ኮርፖሬሽኑ ባለፉት ሰባት አመታት ውስጥ ከ100 በላይ  ፋብሪካዎች ግንባታ ላይ  መሳተፉና በሀገሪቱ በሚገነቡ ሜጋ ፕሮጀከቶች ላይም ከፍተኛ ተሳትፎ እያደረገ ነው ብለዋል

ኮርፖሬሽኑ እስከ አሁን ከ16 ሺ በላይ ተሸከርካሪዎችን በመገጣጠም ወደ ስራ ያስገባ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ለአንበሳ አውቶብስ 500፤ ለሸገር ትራንስፖርት 400 ለፐብሊክ ሰርቪስ 400 የብዙሀን ተሸከርካሪዎችን መስራቱን ያስታወሱት ጄኔራል መኮንኑ ለመኪኖቹ ጥገናና የወርክ ሾፕ ስራዎችን በጋራ እየሰሩ እንደሚገኙ ጠቁመዋል

በ)ለቱ የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንጅነሪንግ የባስ ፕሮዳክሽን ስራ አስኪያጅ የሆኑት ሻምበል ሲሳይ ተሰማ እንደገለጹት በመጀመሪያው ዙር 30 የተማሪ ሰርቪስና 6 ተደራራቢ የከተማ አውቶብሶችን ማስረከባቸውና ቀሪዎቹን በታህሳስ ወር አጠናቀው ለማስረከብ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ከ88 ሰው በላይ የመጫን አቅም ያለው ተደራራቢው የከተማ አውቶብስ አራት ቴሌቭዥን የተገጠመለትና እንደየመንገዱ ሁኔታ ከፍና ዝቅ በማለት ለመጓዝ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ያለው መሆኑንም ገልጸዋል።

ርክክብ የተካሄደባቸው ተሽከርካሪዎች ዘመኑ ያፈራው የጀርመን ሞተር፤ የውጭና የውስጥ ካሜራ የተገጠመላቸው መሆኑን የገለጹት ስራ አስኪያጁ የተማሪ ሰርቪሶቹም ለተማሪዎች ምቾትና ደህንነት ታስበው መሰራታቸውን ጠቅሰዋል።

የቢሾፍቱ አውቶሞቲቪ ኢንዱስትሪ እስከ አሁን ከ2000 በላይ አውቶብሶችን በማምረት በጥቅም ላይ እንዲውሉ ማድረጉንና ኢንዱስትሪው በቀን ከ3 እስከ 4 አውቶብሶችን እየሰራ እንደሚገኙ ሻምበል ሲሳይ ገልጸዋል።

ኮርፖሬሽኑ ለተሽከርካሪዎቹ የመለዋወጫ ችግር እንዳይገጥም ከግል ባለሃብቶች ጋር በጋራ በመስራት ላይ መሆኑና በተጨማሪም ከ280 በላይ በጥቃቅንና አነስተኛ ከተደራጁ ማህበራት ጋርም በትስስር እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

የመከላከያ ብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ባሉት አስራ አራት ኢንዱስትሪዎች ውስጥ ከፍተኛ የስራ እድል ከመፍጠሩም በላይ ከቴክኒክና ኮሌጅ ተመርቀው የሚወጡ ተማሪዎችን ወደ ስራ በማስገባት አቅማቸውን እየገነባ መሆኑን የገለጹት ስራ አስኪያጁ አሁን ያስረከቧቸው ተሸከርካሪዎች የትራንስፖርት ችግሩን ለመቅረፍ የራሳቸውን ድርሻ ያበረክታሉ ብለዋል።

በመጨረሻም የብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ም/ል ዋና ዳይሬክተር ብ/ጅ ጠና ቁሩንዲ ለክቡር ከንቲባው የተሸከርካሪዎቹን ቁልፍ አስረክበዋል።

በርክክብ ስነ ስርሀቱ ላይ የከተማው ም/ል ከንቲባና ጥሪ የተደረገላቸው ሌሎችም የተለያዩ የስራ ሀላፊዎችና የሜቴክ አመራሮችም ተገኝተዋል።

 

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!
በብዛት የተነበቡ የክቡር የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን የህይወት ታሪክ
የክቡር የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን የህይወት ታሪክ
ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ከአባታቸው ከ፲አለቃ መኮንን ይመር አና ከእናታቸው  ከወ/ሮ ሂይወት ይህደጎ ተላ በትግራይ ክልል በሰሜን ምዕራብ ዞን አስገደ ምጽብላ...
ፋውንዴሽኑ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች ሊያስረክብ ነው
ፋውንዴሽኑ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች ሊያስረክብ ነው
የመከላከያ  ፋውንዴሽን  በመጀመሪያ ዙር ያስገነባቸውን 112 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በቅርቡ ለሠራዊቱ በዕጣ ለማስተላለፍ ዝግጅት መጠናቀቁን የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ዋና ስራ...
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ውጤታማ ስራ ማከናወኑ ተገለጸ
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ውጤታማ ስራ ማከናወኑ ተገለጸ
የመከላከያ ኮንስተራክሽን ኢንተርፕራይዝ  በ2011 የበጀት አመት በርካታ ዉጤታማ ስራዎች ማከናወኑ ተገልጿል፡፡
ኮሌጁ ሶስተኛውን ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ አካሄደ
ኮሌጁ ሶስተኛውን ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ አካሄደ
የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ሦስተኛውን ሀገርአቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ አካሄደ።
ሰኔ 14 10 2011 መከላከያ ሬዲዮ ዜና