የኢፌዲሪ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሃመድ ኮሮና ቫይረስን በተመለከተ መንግስት የሰጠውን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው ሰራዊቱን በተመለከተ መግለጫ ስጥተዋል::

የኢፌዲሪ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሃመድ ኮሮና ቫይረስን በተመለከተ መንግስት የሰጠውን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው ሰራዊቱን በተመለከተ መግለጫ ስጥተዋል::

ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሃመድ እንኅደገለፁት የመከላከያ ሰራዊታችን በሃገር ውስጥም ይሁን በሰላም ማስከበር ግዳጆች ላይ ተሰማርቶ የሚገኝ መሆኑን ጠቁመው ተልዕኮውን በብቃት ለመወጣት ራሱን መጠበቅ አለበት::
ሰራዊቱ ሃገርንና ህዝብን ከተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ችግሮች የመከላከል ተልዕኮውን መወጣት የሚችለው ጤንነቱ የተጠበቀ ሲሆን ብቻ እንደሆነ ያብራሩት ጄኔራል አደም የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በየደረጃው ግብረ ሃይል መቋቋሙን ገልፀዋል::

ጄኔራል አደም አያይዘውም ከትቋሙ ባህሪ በመነሳት ሰራዊታችን ግዳን መወጣቱ የሚቀጥል ቢሆንም አዲስ የሰራዊት አባላት ምልመላ: ጊዚያዊ የከተማም ሆነ የቤተሰብ ፍቃድ ለጊዜው መከልከሉን : በሰራዊት ካምፕና መኖሪያ ቤቶች ለደህንነት ሲባል ከውጭ ህብረተሰብ ጋር ያለው ግንኙነቶች እንዲገቱታና መገናኘት እንደማይቻልም አሳስበዋል::
ለደህንነት ሲባል የውጭ ጉዞ ለጊዜው መከልከሉን የጠቆሙት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ ከውጭ በሰላም ማስከበርና በትምህርት ላይ የቆዩትም የምርመራ ስራ ተሰርቶ እንደሚቀላቀሉ ተናግረዋል::