ማሰልጠኛ ማዕከሉ ሙያተኞችን አስመረቀ

በሰሜን እዝ የብ/ ጄኔራል በርሄ ወ/ጊወርጊስ ማሰልጠኛ ማዕከል ያሰለጠናቸውን ሾፌር ሙያተኞች በሙያዊ ክህሎት እና በስነ-ምግባር በማነጽ አስመርቋል፡፡

የሰሜን እዝ ም/አዛዥ ለሎጄስቲክስ ሜ/ጄኔራል ከድር አራርሳ "ሰራዊቱ ሀገራዊና ህገ መንግስታዊ ተልእኮ አንግቦ በተለያየ የግዳጅ ቀጠና የሚገኝ በመሆኑ ትራንስፖርት እና ሌሎች ሎጄስቲክሳዊ ድጋፎችን እንዲያገኝ ወታደራዊ አሽከርካሪዎችን ማፍራት ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው" ብለዋል፡፡

ጄኔራል መኮንኑ አክለውም ተመራቂ አሽከርካሪዎች ያገኙትን አቅም በየጊዜው በማዳበር ለግዳጅ የሚውሉ ተሽከርካሪዎች ለታለመላቸው አላማ ማዋል እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡

የማ/ማዕከሉ ም/አዛዥ ለኦፕሬሽናል ኮ/ል ዘውዱ ጎሹ ስልጠናው በንድፈ ሃሳብ እና በተግባር መሰጠቱን አብራርተዋል፡፡

ተመራቂዎቹ በበኩላቸው በአሰልጣኞች እና በግል ጥረታቸው ለውጤት መብቃታቸውን ገልፀው ቀጣይ በሰለጠኑበት ሙያ አስፈላጊውን አገልግሎት መስጠት እንደሚችሉ አረጋግጠዋል፡፡