የሁርሶ ኮንቴንጀት ሰላም አስከባሪ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት አባላት ለምግብነት የሚውሉትን ጨምሮ ከ20 ሺህ በላይ ሀገር በቀል ችግኞችን በመትከል አሻራቸውን አሳርፈዋል

ሀገራችን ኢትዮጵያ በያዝነው የክረምት ወቅት 5 ቢለዮን ችግኝ ለመትከል የሚያስችል ግብ አስቀምጣ እሰራች ትገኛለች ፡፡ ይህም ሀገራችን በ4 አመት 20 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል  የያዘቸው ራዕይ አካል ነው፡፡

ለዚህ ራዕይ ስኬታማነት የሆርሶ ኮንተንጀት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት አመራሮች ስታፍ አባላት አሰልጣኞች የቅድም  ስምሪት ሻለቆች እና ሻምበሎች በማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ  ውስጥ የተለያዩ ዝርያ ያለቸው ሀገር  በቀል ችግኞችን ተክለዋል፡፡

በዚህ የችግኝ ተላ ፕሮግራም ላይ የራሳቸውን አሻራ ያሳረፉት የሰላም ማስከበር ሎጀስቲክስ ሀላፊ ብርጋዴር ጀነራል ከበደ ረጋሳ ፤ባላፈው አመት ከአሜሪካ ሰራዊት ጋር በትምህርት ቤቱ  ቅጥር ግቢ ውስጥ ችግኝ መትከላቸውን ጠቅሰው፤ሰራዊታችን የሀገራችንን ሰላም እና ደህንንት ከመጠበቅ ባሻገር ሀገራችን የተያያዘችው የአረንዴ ልማት ኢኮኖሚ ከግብ እንዲደርስ  ከመኖሪያ ካምፑ በተጨማሪ ከማህበረሰቡ ጋር በየአካባቢው ችግኝ በመትከል የድርሻውን እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ችግኝ መትከል ድርቅን  በርሀማነትን እና የአፈር መሸርን በመከላከል የተፈጥሮ ሚዛንን ለመጠበቅ ይረዳል ያሉት ጀነራል መኮንኑ ፤ለችግኝ በተሰጠው ትኩረት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱን በደን በመሸፈን ለኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ማድረግ ተችሏል ብለዋል ፤ ሰራዊታችን ችግኝ የመትከል ጥረቱን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው በመጥቀስ፡፡

የሁርሶ ኮንተንጀት ሰላም አስከባሪ  ማሰልጠኛ ትምህረት ቤት አዛዥ ኮሎኔል ዳኘ በላይ በበኩላቸው ከመከላከያ በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ከሀየሎም አርዓያ ወታደራዊ አካዳሚ እና ከምዘና ማዕከል ጋር በመቀናጀት ለምግብነት የሚውሉ ዛፎችን ጨምሮ ከ20 ሺህ በላይ ሀገር በቀል ችግኞችን ተክለናል ብለዋል፡፡

አካባቢው በቂ ዝናብ የማያገኝ በመሆኑ  ችግኞቹ እንዳይደርቁ የውሀ ቦቴ መኪኖችን ከማዘጋጀት ጀምሮ የውሀ ሮቶዎችን እና የውሀ ማስተላለፊያ ቱቦዎችን ገዝተናል ያሉት ኮ/ል ዳኘ ፣ ችግኞቹ አድገው የሚፈለገውን ጥቅም እንዲሰጡ የግቢው አባላት የእንክብካቤ ስራ እንዲሰሩ ይደረጋል ብለዋል፡፡

ችግኝ በመትከል የተሳተፉት የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ የሰራዊት አባላት በሰጡት አስተያያት ችግኝ መትከል ታላቁን የህዳሴ ግድብ በደለል እንዳይሞላ ከመከላከል በተጨማሪ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የሚመጡ ችግሮችን ለመቆጣጠር  እደሚያስችል በመጠቆም የተከሏቸው ችግኞች አድገው ለፍሬ እስከሚበቁ በመኮትኮት እና ውሀ በማጠጣት በዘላቂነት ለመንከባከብ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል ፡፡

የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ አባላት ባለፈው አመት የተከሏቸውን ችግኞች በመንከባከባቸው ችግኞቹ ከፍተኛ የልምላሜ ደረጃ ላይ መድረሳቸውንም ተናግረዋል፡፡