የጦር ሃይሎች ጠ/ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሃመድ ፣ አዲሱ የመከላከያ ሰራዊት የግንባታ ስትራቴጂ ሰራዊቱ ከወገንተኝነት በጸዳ መልኩ ተልእኮውን እንዴት መፈጸም እንዳለበት ግልጽ አቅጣጫ ያስቀመጠ መሆኑን ተናገሩ ፡፡

 

ነሀሴ 7 ቀን 2012

የኢፌዴሪ የመከላከያ ሰራዊት በመፈጸም ላይ የሚገኘውን ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ተልእኮ ዘመኑ ከሚጠይቀው የተሟላ ወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ ጋር ራሱን በማብቃት ውጤታማ የግዳጅ አፈጻጸም እያስመዘገበ እንደሚገኝና በተቋማዊ ሪፎርሙ እንደ ግብ የተቀመጡ የዘመናዊ ሠራዊት ግንባታ ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን አስረድተዋል ፡፡

እንደ ጄኔራል አደም መሃመድ ገለጻየኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት አለም አቀፋዊና ከባቢያዊ ሁኔታን ከግምት ውስጥ ያስገቡ የሳይበርና የባህር ሃይል አዳዲስ አደረጃጀቶችንም በተቋሙ ውስጥ ተግባራዊ በማድረግ የተሄደበት ርቀት ከፍተኛ ነው፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት በአሁኑ ወቅት ከመቼውም ጊዜ በላይ የአስተሳሰብ አንድነት በመፍጠር ህገመንግስታዊ ተልእኮውን በላቀ ብቃት ለመፈጸም በሚያስችል የተሟላ የዝግጁነት ቁመና ላይ እንደሚገኝ ያብራሩት የጦር ሃይሎች /ኢታማዦር ሹሙ ጄኔራል አደም መሃመድ ፣ በአዲሱ የመከላከያ ሰራዊት የግንባታ ስትራቴጂ መጽሐፍ ላይ የተካሄደው ስልጠናም ሰራዊቱ ከወገንተኝነት በጸዳ መልኩ ተልእኮውን እንዴት መፈጸም እንዳለበት ግልጽ አቅጣጫ ያስቀመጠ ሰነድ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ወንድማገኝ ታደሰ

ፎቶግራፍ  አብዱልውሀብ ሙህዲን