በሱዳን ፣ አቢዬ ሰሜን ሴክተር ፣ ለሁለት አመታት በአለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ተልእኮ ግዳጁን በጀግንነት ሲወጣ የነበረው 20ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ ለተተኪው 23ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ ግዳጁን አስረከበ

በሱዳን ፣ አቢዬ ሰሜን ሴክተርለሁለት አመታት በአለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ተልእኮ ግዳጁን በጀግንነት ሲወጣ የነበረው 20 ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ ለተተኪው 23 ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ ግዳጁን አስረከበ ።


በርክክብ ስነስርአቱም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት UNISFA የበላይ ጠባቂና የተልእኮው የሀይል አዛዥ / ከፍያለው አምዴ እና ምክትል ሀይል አዛዡ / ነጋሲ ትኩዬ ከስታፎቻቸው ጋር ተገኝተው ለሁለቱም ሻለቆች መልእክት አስተላልፈዋል።


ለሁለት አመታት በቁርጠኝነትና በፍጹም ኢትዮጲያዊ ጨዋነት ግዳጃችሁን በመወጣት ሀገራችሁን ላኮራችሁ 20 ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አባላትና በየደረጃው ላላችሁ አመራሮች ምስጋናዬን እያቀረብኩ ለተተኪ ወንድሞቻችን 23 ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አባላትና አመራሮችም መልካም የስራ ጊዜ እመኝላችኋለሁ ብለዋል ።