በዩኔስፋ ኃይል አዛዥ የተመራው ልዑክ የሠራዊቱን የግዳጅ ቀጣና ጎበኘ

 

በሱዳን አብዬ በዩኔስፋ ኃይል አዛዥ ሜጄር ጄኔ ራል ገብረ አድሃና  የተመራው ከፍተኛ የዩኔስፋ የሥራ ኃላፊዎች የሱዳንና ደቡብ  ሱዳን ናሽ ናል ሞኒተር አመ ራሮች የያዘው ቡድን የ3ኛ ዙር ቦርደር ጥበቃ ሻለቃ አባላት የተሰማሩበትንና ትሽዊን ተብሎ የሚ ጠራው ጊዜያዊ ቲም ሳይት ጎበኙ።

የጉብኝቱ ዓላማ ከሬጅመንት አባላት ጋር ለመተዋወቅ፣ በቀጣይ አዳዲስ ቲም ሳይቶች መክፈት ስለሚቻልበት ሁኔታ ለማመቻቸትና በእስካሁኑ በሁለቱም ሀገራት የተገባውን ስምምነት በተመሰረተው ጊዜያዊ ቲም ሳይት እንዴት እየተተገበረ እንዳለ ለማወቅ መሆኑን የተናገሩት ሜጄር ጄኔራል ገብረ፣ ከተደረገው ጉብኝትም በሁለቱም ሀገሮች በኩል በስምምነቱ መሠረት በመሄድ በኩል ውስንነት እንዳለ መመልከታቸውንና ይህ ችግርም ስምምነቱን የሚሰጥ አካሄድ በመሆኑ ችግሩን ለመፍታት በቀጣናው ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የሁለቱም ሀገራት አመራሮችና ሌሎች አካላት ጋር በመነጋገር ለመፍታት ጥረት እንደሚደረግ አስረድተዋል።

በግዳጅ ቀጣናው የተሰማሩት የሠራዊታችን አባላትም የነበረውን የመጠለያ፣ የውሃ እና ሌሎች ችግሮች በመቋቋምና እራሳቸውም ችግሩን ለመፍታት ጥረት በማድረግ ያሳዩት ከፍተኛ ጥረት የሚደነቅ መሆኑን አስታውቋል።

የኃይል አዛዡ በቀጣይ በሬጅመንትም ይሁን በጊዜያዊ ቲም ሳይቱ  አስፈላጊ አገሮች እንዲሟሉ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር አቅም በፈቀደ መልኩ ለመፍታት እንሰራለን። በፀጥታ በኩልም አንዳንድ በቡድንና በግል የሚንቀሳቀሱ አካላት ስለሚኖሩ አካባቢን መቃኘትና ሁሌም ዝግጁ መሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።

የ3ኛ ቦርደር ጥበቃ ሻለቃ ዋና አዛዥ ኮሎኔል አለነ ፀጋይ በበኩላቸው፤ በካዳጉሊ ስለሬጅመንቷ ግዳጅና በትሽዊን ጊዜያዊ ቲም ሳይት ስላለው አጠቃላይ ሁኔታ፤ በቲም ሳይቱ ስለተሰሩ ስራዎችና በቀጣይ መሟላት ስላለባቸው ነገሮች ገለጻ አድርጓል።

 

ትምህርት ለሠራዊቱ ዝግጁነትየማይተካ ሚና እንዳለው ተገለጸ

 

ለዘመናዊ ሠራዊት ግንባታ የአካዳሚ ትምህርት የማይተካ ሚና እንዳለው  ተገለጸ።

በዚሁ መሠረት በባሩድ ማዕከላዊ ዕዝ በ33ኛ ክፍለ ጦር ለዘመናዊ ሠራዊት ግንባታ ወሳኝ በሆነው በአካዳሚ ትምህርት ዙሪያ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች እንደሚሰሩ ተገለጸ።

የክፍለ ጦሩ አጠቃላይ ትምህርት ዴስክ አስተባባሪ ሻምበል አይፈራም የሺብር እንደተናገሩት፤ ተቋሙ ሠራዊቱ በአካዳሚ ዕውቀቱ የበለፀገና የአመራርነት ሚናውንና የታጠቅናቸውን ትጥቆች በዕውቀት ላይ ተመስርቶ ይጠቀመው ዘንድ የትምህርት ተደራሽነት በማስፋፋት እንደሚሰራ ሁሉ እኛም እንደክፍለጦሩ የሠራዊቱን ዕውቀት አድማስ ለማስፋትና ለዘመናዊ ሠራዊት ግንባታ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እንሰራለን ብለዋል።

ከመምህራኖች መካከል መምህር ገ/መስቀል በርሄ እና ርዕሰ መምህር ዳንኤል ገ/መድህን በሰጡት ተመሳሳይ አስተያየት የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ለትምህርት ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ ሠራዊቱም ጥሩ የትምህርት አቀባበልና ዕውቀትን የመቅሰም ችሎታ ያለው በመሆኑ የሚያኮራ ሠራዊት ነው ብለዋል።  የዘገበው  የክፍለ ጦሩ ሪፖርተር ፶አለቃ እንግዳው ታደሰ ነው።

በተያያዘ ዜና በባሩድ ማዕከላዊ ዕዝ የ22ኛ ንስር ክፍለ ጦር የአካዳሚ ትምህርት አፈጻጸም ውጤታማ እንዲሆን ለተማሪዎች የተጠናከረ ድጋፍ እየተሰጠ እንደሚገኝ ተገለጸ።

የክፍለ ጦሩ አጠቃላይ አካዳሚ ትምህርት ዴስክ ኃላፊ ሌ/ኮሎኔል ፍትሃ ነገስት አብርሃ የትምህርት አፈጻጸም አስመልክተው እንደገለጹት፤ በክፍለ ጦሩ የአካዳሚ ትምህርት የመማር ማስተማሩ ሂደት ከመደበኛ እስከ ርቀት የትምህርት መርሀ-ግብር እየተሰጠ ሲሆን፤ በመደበኛ ትምህርት ተመዝግበው ለሚማሩ አባላት ከሠራዊቱ በተውጣጡ እና ልምድ ባካበቱ መምህራን የታገዘ ትምህርት የሚሰጥ መሆኑን ገልጸው፣ አፈጻጸሙ ውጤታማ እንዲሆን ተመዝግበው ትምህርታቸውን ለሚከታተሉ የሠራዊት አባላት የተጠናከረ ድጋፍ ይሰጣል ብለዋል።

ሌተና ኮሎኔሉ አያይዘውም፤ ሠራዊቱ ከዘመኑ ጋር እየዘመነ የሚጓዝ እንደመሆኑ በየደረጃው ያለ አመራር ለትምህርት ትኩረት በመስጠት ሠራዊቱ ራሱን በዕውቀት  እንዲገነባ በማድረግ እየሰራ ነው።

ሠራዊቱም ትምህርት ሁለንተናዊ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን በመገንዘብ ሁሉም መማር ማንበብ የሚለውን መርህ መያዝ አለበት ማለታቸውን የክፍለ ጦሩ ሪፖርተር ፲ አለቃ አብርሃም ጥላሁን ዘግቧል።

 

      ሠራዊቱ የህዳሴ ግድብን ግንባታ ጎበኘ

በአበበ ሰማኝ (!አለቃ)

የዕዙ ሪፖርተር

የባሩድ ማዕከላዊ ዕዝ የሠራዊት አባላት ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ጎበኙ።

በወቅቱ ለሠራዊቱ ገለፃ የሰጡት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ እንደተናገሩት፤ በሀገራችን የሚከናወኑ ሁለንተናዊ የልማት ክንውኖች ያለምንም እንቅፋት እንዲቀጥሉ ሠላም ቀዳሚ ተግባር ነው። የሀገራችን የሠላም ጉዳይ ሲወሳ ደግሞ የመከላከያ ኃይላችን ቅድሚያ ቦታውን ይይዛል። እናም ለዘመናት ህዝቦች የሚናፍቁትን ታላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክት ማሳለጫ ግብዓት በመሆኑ ለጀግናው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ታላቅ ክብር ይገባዋል ብለዋል።

የጉብኝቱ አስተባባሪ ኮሎኔል ገብረዮሐንስ ገብረ በበኩላቸው፤ ሠራዊቱ ከህዝብ አብራክ የወጣ እና ለህዝብ የቆመ ኃይል መሆኑን ከሚያረጋግጥባቸው ልማታዊ ክንውኖች ውስጥ አንዱ የሆነው ታላቁ የህዳሴ ግድብ በሚፈለገው መንገድ እንዲከናወን እና የሀገራችን ህዝቦች ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ለማስቻል የመከላከያ ኃይል የሚጠበቅበትን ሁሉ ለመወጣት ቁርጠኛ ነው ብለዋል።

የሠራዊት አባላቱም በጉብኝቱ ወቅት የሀገራቸው የህዳሴ መሠረት የሆነው ይህ ፕሮጀክት ያለበትን ሁኔታ መመልከታቸው ሀገራዊ ስሜትን ይበልጥ እንደሚያጎለብት እና ለሚሰጡት ተልዕኮዎች ተጨማሪ አቅም እንደሚሆናቸው ተናግረዋል።