በደቡብ ሱዳን ጁባ ሴክተር የተሰማራው የ12ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ የመሃንዲስ አባላት አበረታች ተግባር እያከናወኑ መሆኑ ተመለከተ፡፡

የሻለቃው የስራ መሃንዲስ ሃላፊ ሻ/ል መሃመድ መንገሻ ፣ ሻለቃው ወደ ደቡብ ሱዳን ጁባ ከተሰማራበት ጊዜ አንስቶ የመሃንዲስ ክፍሉ ያከናወናቸው ተግባራት ሰራዊቱ የዕለት ከዕለት ስራው የተሳካ እንዲሆን ማስቻሉን ተናግረዋል፡፡

የሰራዊቱን ኑሮ ምቹ ከማድረግ አንፃር መመገቢያ አዳራሽና የምግብ ማብሰያ ቤት በመገንባት ፣ ጀነሬተሮች ብልሽት እንዳያጋጥማቸው ንፅህናቸውን በመጠበቅና ከመበላሸታቸው በፊት የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎችን በማከናወን እንዲሁም ብልሽት በሚያጋጥም ጊዜ ተከታትሎ የጥገና ስራዎችን በመስራት ለሰራዊቱ ግዳጅ ስኬት ትልቅ ድርሻ እየተወጣ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

የውሃ ማጣሪያዎችና ማጠራቀሚያዎች ንፅህናቸው የተጠበቀ ኢንዲሆን እና በቂ አቅርቦት እንዲኖረው በዕለት ከዕለት ክትትል በማድረግ እና ኮቪድ-19ን ለመከላከል እየተወሰዱ ያሉትን የመከላከል ስራ የተሳካ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል ፡፡