የመከላከያ መርሆዎች

 1. የሀገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና የህዝቦች ሚዛናዊ ተዋጽኦ ያካተተ ይሆናል::
 2. የመከላከያ ሚኒስትር ሆኖ የሚሾመው ሲቪል ይሆናል::
 3. የመከላከያ ሠራዊት የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ከመጠበቅ በተጨማሪ በዚህ ሕገ-መንግስት መሰረት በአቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚሰጡትን ተግባሮች ያከናዉናል::
 4. የመከላከያ ሠራዊቱ በማንኛውም ጊዜ ለሕገ-መንግስት ተገዥ ይሆናል::
 5. የመከለከያ ሠራዊቱ ተግባሩን ከፖለቲካ ድርጅቶች ወገናዊነት ነፃ በሆነ አኳኋን ያከናውናል::

ለሕገ-መንግስታዊ ሥርዓቱ ፍጹም ታማኝ የሆነ፣ የሀገራችን ህዝቦች ተምሳሌት የህዝብ አመኔታና ፍቅርን የተጎናጸፈ፣ የዕውቀት መፍለቂያ፣ ጦርነትን ማስቀረት የሚችል፣ ካጋጠመ በአስተማማኝ የማሸነፍ ብቃት ያለው፣ በአህጉራዊና በዓለም አቀፋዊ ግዳጅ ግንባር ቀደም ሚና የሚጫወት ዘመናዊ የመከላከልያ ኃይል ተገንብቶ ማየት::

 • ሀገሪቱንና ሕገ-መንግስታዊ ሥርዓቱን ከውጭ ወራሪ ኃይሎች፣ ሽብርተኞችና ከውስጥ ፀረ-ሠላም ኃይሎች በአሰተማማኝ ሁኔታ በመከላከል የሀገሪቱ ሠላም እንዲጠበቅና የፈጣን ልማትና የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እንቅስቃሴ ያለ እንቅፋት እንዲቀጥል ማድርግ፤
 • አግባብነት ያላቸው የክልል መስተዳደር የደህንነት እና የፀጥታ መዋቅሮችን የደህንነትና የፀጥታ ማስከበር አቅማቸውን መገንባትና ከእነርሱ ጋር ተቀናጅቶ መስራት፤
 • የሀገሪቱን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች፣ የህዝብና የመንግስት የልማት ተቋማትንና አውታሮችን ከማንኛውም ሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ አደጋዎች መከላከልና ማዳን፤
 • ሀገራዊ ደህንነትን ማረጋገጥና በአከባቢያዊ፣ አህጉራዊና አለም አቀፋዊ የሠላም ማስከበር ተልዕኮዎች ላይ በብቃት መሳተፍ::
 • ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፤
 • ምን ጊዜም የተሟላ ስብዕና፤
 • ያልተሸራረፈ ዲሞከራሲያዊ አስተሳሰብ፤
 • በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።