ማስታወቂያ

የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል

 

2. የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቾች መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለፀ ፡-

     ለጤና ሳይንስ ኮሌጅ የትምህርት መስክ

 • የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ የሆነ/የሆነች
 • ለሜዲሲን/ለዶክትሬት ዲግሪ የ2011 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ውጤት ለወንድ 475 ለሴት 465 ውጤት ያለው/ ያላት ወይም ትምህርት ሚኒስቴር የህክምና ዶክትሬት ዲግሪ ለማጥናት በሚያስቀምጠው የመነሻ ውጤት መሰረት ወይም ተቀራራቢ ውጤት ያለው/ያላት
 • በመጀመሪያ ዲግሪ ደረጃ በጀነሪክ ፕሮግራም ለሚሰጡ የጤና ትምህርቶች ወይም ዲፓርትመንቶች የወቅቱን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው የማለፊያ ነጥብ ለወንድ 350 ለሴት 335 ውጤት በማምጣት ትምህርት ሚኒስቴር የሚያስቀምጠውን ውጤት ማሟላት የሚችሉ
 •  ለታዳጊ ክልል አመልካቾች በመጀመሪያ ዲግሪ ደረጃ በጀነሪክ ፕሮግራም ለሚሰጡ የጤና ትምህርቶች ወይም ዲፓርትመንቶች የወቅቱን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው ለወንድ 335 ለሴት 320 የማለፊያ ውጤት ያላቸው
 • ለታዳጊ ክልል ሜዲሲን አመልካቾች ለወንድ 460 ለሴት 450
 •  ለግል ተፈታኞችና አመልካቾች ለጤና የትምህርት መስኮች ለወንድ 365 ለሴት 360  መግቢያ ውጤት ማሟላት የሚችሉ
 • ለሜዲሲን ለግል ተፈታኞችና አመልካቾች ለወንድ 500 ለሴቶች 490 እና ከዚያ በላይ
 • ትምህርታቸውን እንደ አዲስ ማጥናት የሚፈልጉ

 

   ለኢንጂነሪንግ ኮሌጅ የምልመላ መስፈርቶች          

 

 • የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ የሆነ/የሆነች
 • የወቅቱን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስዶ/ወስዳ ለወንድ ውጤቱ 350 እና ከዚያ በላይ ለሴት ውጤቷ 335 እና ከዚያ በላይ የሆነና መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በሚያወጣው የመቁረጫ ነጥብ
 • ከታዳጊ ክልሎች ለሚመጡ አመልካቾች የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው ውጤታቸው ለወንድ 335 ለሴት 320 እና ለግል ተፈታኞችና አመልካቾች ለወንድ 365 ለሴት 360
 • ለሁሉም አመልካቾች የ10ኛ ክፍል ውጤት በእንግሊዘኛ፣በሂሳብ፣በፊዚክስና ኬሚስትሪ “C” እና ከዚያ በላይ ያላቸው
 • ዘጠነኛ እስከ አስረኛ ክፍል ድረስና ከ11ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያለውን ወይም የመሰናዶ ትምህርት ውጤት ትራንስክሪፕት ዋናውንና ኮፒ ማቅረብ የሚችል/የምትችል
 • ሴቶች ዩኒቨርሲቲው በሚያወጣው የመቀበያ ነጥብ መሰረት ይበረታታሉ

 

ማሳሰቢያ ፦ከላይ የተዘረዘሩት መስፈርቶች እንደ ተጠበቁ ሆነው በተጨማሪም የውትድርና ሙያን መስፈርት የሚያሟላ/የምታሟላ  እንዲሁም ወታደር ለመሆን ሙሉ ፈቃደኛ የሆነ/የሆነች

 

 

የምዝገባ ጊዜ፡- ከህዳር 1 እስከ ህዳር 25 ቀን 2011 ዓ.ም ወታደር ለሆናችሁ

ስቪል(ምልምል) ለሆናችሁ ከህዳር 1 እስከ ህዳር 25 ቀን 2011 ዓ.ም  

የምዝገባ ቦታ፡- ለአዲስ አበባ  አመልካቾች ምድር ሃይል ተጠጠባባቂ

ለክልል አመልካቾች፡- በክልልና ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም በሁሉም በቀበሌዎች ይካሄዳል 

የማመልከቻ ቀን :  Mar 01, 2011 03:00  ‐  Mar 25, 2011 03:00

ድረ ገጽ :  https://www.fdremod.gov.et


ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!